በዳሰሳ ጥናቶች ገንዘብ ያግኙ
ትርፍ ጊዜ አለዎት? ጊዜዎትንስ ትርፍ ጊዜ አለዎት? ጊዜዎትንስ ሊጠቀሙበት ይፈልጋሉ?
በ ቲጂኤም ፓነል ኢትዮጵያ ላይ በነጻ ይመዝገቡና
እርስዎ በትክክለኛው ቦታ ላይ ነዎት!
አሁኑኑ ይመዝገቡና ክፍያ ባላቸው የዳሰሳ ጥናቶች በመሳተፍ ዓለም አቀፉን ገበያ የተሻለ ለማድረግ ያግዙን!
ራሳችሁን እንድትገልጹ እድል የሚሰጠውን ቲጂኤም የገበያ ጥናት መድረክ ይቀላቀሉ። በአለም ዙሪያ ያሉ ኩባንያዎች እርስዎ እንደ ሸማች ምን እንደሚያረካዎት እና ምን እንደሚያስከፋዎት ለማወቅ እርስዎን እየጠበቁ ነው።
አለም በለውጥ ወስጥ ባለችበት ወቅት ዝም ብለው አይቀመጡ፣ ክፍያ ባላቸው የዳሰሳ ጥናቶች ,ይሳተፉ!
የዳሰሳ ጥናቶቻችንን አስደሳች እና ለመሙላት ቀላል እንዲሆኑ አድርገን ነው የምንሰራው። የዳሰሳ ጥናቶቻችን እርስዎ እንደ ሸማች እንዲሻሻሉም ይረዳዎታል። ለመሳተፍ የሚያስፈልገው ማንኛውም መተግበሪያ መሳሪያ እና ኢንተርኔት ማግኘት ብቻ ነው!
ለምን ይቀላቀሉን?
ክፍያ ያላቸው የሞባይል ዳሰሳዎች
የተሻለ ገበያ መኖሩ በራሱ ሽልማት ነው፣ ነገር ግን ለጥረትዎ ክፍያ ማግኘት አይጎዳም። በተሳካ ሁኔታ ለሚያጠናቅቁት እያንዳንዱ የዳሰሳ ጥናት እስከ 3.25 የአሜሪካ ዶላርያገኛሉ።
የግል መረጃ ደህንነት እና ሚስጥራዊነት
እርስዎ የሚያቀርቡት ማንኛውም መረጃ ሚስጥራዊ እና የተጠበቀ ይሆናል። ያለፍቃድዎ የግል መልስዎትን ለማንም አንገልጽም።
ምንም ድብቅ አላማ አይኖረንም
ምንም ድብቅ ነገር የለም! የአለምአቀፍ ማህበረሰባችንን መቀላቀል ሙሉ በሙሉ ነፃ ነው። አሁኑኑ ይመዝገቡ እና በኦንላይን ገንዘብ ያግኙ!
በማንኛውም ቦታ፣ በማንኛውም ጊዜ፣ ማንኛውም መሣሪያ!
ማንኛውንም መሳሪያ በመጠቀም፣ በማንኛውም ጊዜ እና ከየትኛውም ቦታ ሆነው የዳሰሳ ጥናቶችን ይውሰዱ፡ ስማርትፎን ፣ ላፕቶፕ ወይም ታብሌት። ኢትዮጵያ ውስጥ ክፍያ ካላቸው የዳሰሳ ጥናቶች ገቢ ለማግኘት የሚያስፈልግዎት ከበይነመረብ ወይንም ኢንተርኔት ጋር መገናኘት ብቻ ነው።
ሽልማትዎን ማግኘት ቀላል ነው።
ክፍያዎን 12.50 ዶላር ከሰበሰቡ በኋላ በ ፔይፓል በኩል ወይም በ ጂኮድስ በኩል 10 ዶላር በሂሳብዎ ከሰበሰቡ በኋላ መቀበል ይችላሉ።
ለእርስዎ አስተያየት ዋጋ እንሰጣለን
የሚወዷቸው ብራንዶች አቅርቦታቸውን ለማሻሻል ሲሉ እርስዎ ስለምርቶቻቸው እና አገልግሎቶቻቸው ምን እንደሚያስቡ ለመስማት ጓግተዋል።
በጋራ አወንታዊ ለውጥ ማምጣት
ጥረታችንን መቀላቀል በአለም አቀፍ ገበያ ላይ የማያቋርጥ መሻሻል እንዲኖር ለምናደርገው ግፊት ጉልበት ይሰጠናል። እርስዎ ክፍያ ባላቸው የዳሰሳ ጥናቶች ላይ በመሳተፍና የበኩላችሁን በመወጣት፣ እኛም በበኩላችን ግብአትዎን ከ100 በላይ ከሆኑ የአለም ብራንዶች ጋር በማገናኘት፣
የመረጃ ደህንነት ከፍተኛ ቅድሚያ ከምንሰጣቸው ነገሮች አንዱ ነው
የእርስዎ መረጃ 100% ደህንነቱ የተጠበቀ እና በሚስጥር የተያዘ ነው
ከ ቲጂኤም ፓነል ደንበኝነት መውጣት ለደንበኝነት መመዝገብ ያህል ቀላል ይሆናል፣ በማንኛውም ጊዜ ለመውጣት ነፃ ነዎት
በማንኛውም ጊዜ ከደንበኝነት ምዝገባ ለመውጣት ነፃ ነዎት
የአጠቃላይ መረጃ ጥበቃ ደንብ (ጂዲፒአር/ GDPR) እና የ ኢሶማር(ESOMAR) ደንቦችን እናከብራለን
ክፍያ ያላቸውን የዳሰሳ ጥናቶች መውሰድ ጥቅሙ ምንድነው?
በቤት የሚወሰዱ ክፍያ ያላቸው ዳሰሳ ጥናቶች አስቸጋሪ አይደሉም፤ መልስ ለመስጠት ባላቸው ግልጽነትና እና ቅለት ይለያሉ። እነሱን መውሰድ ብዙውን ጊዜ ከጥቂት ደቂቃዎች በላይ አይወስድም።
ምንም እንኳን ክፍያ ያላቸው የዳሰሳ ጥናቶችን ከሚሰጡ የምርምር ፓነሎች በአንዱ ላይ ተመዝግበን ቢሆንም፣ አሁንም ተጨማሪ ፓነሎችን መቀላቀል እንችላለን። በወሰድናቸው ዳሰሳ ጥናቶች መጠን ገቢያችን ስለሚጨምር ይህ በጣም ጥሩ ዘዴ ነው።
የዳሰሳ ጥናቶቹ ብዙ ጊዜ በአካባቢው ገበያ ላይ ስለሌሉ አገልግሎቶች እና ምርቶች ይጠይቃሉ። ይህ ስለ አዳዲስ ነገሮች የበለጠ ለማወቅ እድል ይሰጠናል።
በዳሰሳ ጥናት በኩል የምንገልጸው አስተያየት የኩባንያውን ምርቶች እና አገልግሎቶች የተሻለ ማድረግ ላይ ተጨባጭ የሆነ ተጽእኖ አለው፤ ከዳሰሳ ጥናት ዝግጅት ጀርባ ያለው አንዱ ምክንያት ይህ ነው። የዳሰሳ ጥናቶች ገቢ ክፍያችንን ብቻ ሳይሆን የግል እርካታንም ይሰጠናል።
የቲጂኤም ፓነል ምንድን ነው እና በእሱ እርዳታ የኦንላይን እና የሞባይል ዳሰሳ ጥናቶችን መውሰድ እንዴት ይቻላል?
በይነመረብ ላይ በቀላሉ ገንዘብ እንዴት ማግኘት ይቻላል?
የመጀመሪያው እርምጃ በጣም ጥሩ ከሆኑ የዳሰሳ ጣቢያዎች አንዱ በሆነው ድረ-ገፃችን ላይ መመዝገብ ነው። መመዝገብ መሰረታዊ መረጃዎን በተለይም፡ የኢሜል አድራሻዎን፣ የልደት ቀንዎን እና ጾታዎን መሙላትን ያጠቃልላል። እባክዎ ያስታውሱ የሚሰጠው መረጃ ትክክለኛ መሆን አለበት - ይህም ቀለል ያለ የመረጃ እና የገንዘብ ፍሰትን ያረጋግጣል። ወደ https://portal.tgmpanel.com በመሄድ በፓነሉ ድህረ ገጽ ወይም በተጠያቂው ፖርታል መመዝገብ ይቻላል።
ሁለተኛው እርምጃ ማንነትዎን ማረጋገጥ እና በድረ-ገጹ ላይ መመዝገብ ነው። መረጃዎትን ለማረጋገጥ በኢሜል የተላከልዎትን ሊንክ መከተል አለብዎት። እባክዎ የማረጋገጫ ኢሜይሉን ማግኘት ካልቻሉ የማስተዋወቂያዎችን እና የስፓም መልዕክት ማህደርዎ ውስጥ መፈለግዎን ይረጋግጡ።
ኢሜይሎቻችን ወደ የመልዕክት ሳጥንዎ እንጂ ወደ አይፈለጌ ወይም ስፓም መልእክት እንዳይሄዱ ለማረጋገጥ፣እባክዎ ወደ አድራሻዎ ዝርዝር ወይም አድራሻ ደብተር ያስገቡት።
አራተኛው ደረጃ ምርጥ የሚከፈልባቸው የዳሰሳ ጥናቶችን መጠባበቅ ነው። ከፕሮፋይልዎ ጋር የሚስማማ ጥናት ሲኖር፣ ብዙ ጊዜ በኢሜይል ማሳወቂያ ይደርሰዎታል። በዚህም መንገድ በእኛ ኦንላይን ፓነል ላይ ሂሳብዎን ለመጨመር እድሉን ያገኛሉ። ይህ በጥናቱ ጊዜያዊነት
ስለ ሁሉም የዳሰሳ ጥናቶች በኢሜል እንደማናሳውቅ ያስታውሱ እና አንዳንድ ማሳወቂያዎችም በሌሎች መልእክቶች ብዛት ውስጥ ሊጠፉ ይችላሉ ፣ ስለሆነም የእለት ተእለት ልምድን በማዳበር ለምሳሌ በማለዳ ቡና ጊዜ ፣ ወደ መልስ ሰጪዎ ፓነልhttps://portal.tgmpanel.com - በመግባት ለመሙላት ዝግጁ የሆኑ አዳዲስ የዳሰሳ ጥናቶች መኖራቸውን ማረጋገጥ ጥሩ ነው (ማለትም የተወሰነ ገንዘብ ኦንላይን ለማግኘት እድሉ መኖሩን ለማረጋገጥ)።
እንዲሁም አዳዲስ የዳሰሳ ጥናቶችን በዋትስአፕ እና በፌስቡክ ሜሴንጀር አፕሊኬሽን እና ክሮም ፕላግኢንስ ማሳወቂያዎችን መቀበል ይችላሉ፤ የዳሰሳ ጥናቱ በቀጥታ በስልክዎ ላይ ወይም በኮምፒውተርዎ ስክሪን በኩል እንዲታይ ማለት ነው። እነዚህ አማራጮች በ https://portal.tgmpanel.comምርምር ፓነል አካውንትዎ ላይ ባሉ ማስተካከያዎች ውስጥ ሊበሩ (እና በቀላሉ ሊጠፉ ይችላሉ)።
አምስተኛው እርምጃ የዳሰሳ ጥናት ማድረግ ነው። በድጋሚ፣ የሚሰጡት መልሶች ታማኝ እና የታሰበባቸው ሊሆኑ እንደሚገባ አስታውሱ። ያስታውሱ - ኦንላይን ከእኛ ጋር የሚሰሩት የዳሰሳ ጥናቶች ስራ ፣ እንዲሁም በተለያዩ ኩባንያዎች በታዘዙ የገበያ ጥናት ምርምሮች ውስጥ የሚሰጡት ግብዓት ያለው አስተዋጽኦ በጣም አስፈላጊ ነው። በእነዚህ የዳሰሳ ጥናቶች ላይ በመመስረት፣ በእርስዎ ህይወት ላይም ተጽእኖ ሊያሳድሩ የሚችሉ ጠቃሚ ውሳኔዎች ይካሄዳሉ። ታማኝ መልሶችን በመስጠት በፓነላችን ላይ ያሉ ክፍያ ያላቸው ኦንላይን የዳሰሳ ጥናቶችን እንዳጠናቀቁ፣ ሙሉ በሙሉ ሚስጥራዎነታቸው የሚጠበቅ ስለሆነ ምንም የሚያስጨንቅ ነገር አይኖርም።
የዳሰሳ ጥናት ከጨረስን በኋላ ምን ያህል ገቢ እንዳገኘን ማረጋገጥ እንችላለን። የቲጂኤም ፓነል ለተወሰደው የዳሰሳ ጥናት በ አሜሪካን ዶላር እና ነጥቦች ገቢ ገንዘብ ያቀርባል (1 ነጥብ= 1 አሜሪካን ዶላር )። እንዲሁም ለምርምሩ ብቁ ካልሆኑ (የተዘጋ የዳሰሳ ጥናት፣ ሙሉ ኮታ፣ የተለየ ምላሽ ሰጪ ፕሮፋይል ያስፈልጋል፣ ወዘተ.)፣ ለጠፋው ጊዜ 0.02 ነጥብ ያገኛሉ።
ስድስተኛው እርምጃ ክፍያዎን መቀበልን ሰለሚያካትት በጣም ጥሩው እርምጃ ነው። ለዝውውር የሚያስፈልገውን አነስተኛውን መጠን ማረጋገጥዎን ያስታውሱ። በቲጂኤም ፓነል፣ ያ መጠን ለአሜሪካን ዶላር ክፍያዎች 10 አሜሪካን ዶላር ወይም በነጥብ ሂሳብ ክፍያ 3.5 ዶላር ይሆናል (አንዳንድ ጥናቶች የሚከፈሉት በዶላር ነው፣ አንዳንዶቹ ደግሞ በነጥቦች ተከፍለው በኋላ ወደ ዶላር ይቀየራሉ - እንደ ደንበኛው ሁኔታ)።
የቲጂኤም ፓነልን ጨምሮ ሌሎች ፓነሎች በ ፔይፓል በኩል ገንዘብ ያዘዋውራሉ- paypal.com። በኋላ ላይ ክፍያውን ከ ፔይፓል ሂሳብ ወደ መደበኛ የባንክ ሂሳብ ማስተላለፍ እንችላለን። ከጥቂት ቀናት በኋላ ገንዘባችን በመድረሻው ሂሳብ ላይ ይገኛል።p>
እንዲሁም የተገኘውን ገቢ የስልክ ሂሳብዎን ለመሙላት (የሚሞላ ስልክ ባለቤት ከሆኑ) መጠቀም ይቻላል።
ሦስተኛው የክፍያ ዘዴ የ ጂኮድስ የስጦታ ኮዶችን በመጠቀም ነው - ተጨማሪ መረጃ በ app.gcodes.com ላይ ይገኛል።
ፓነሉን አሁን ይቀላቀሉ!
ቀላል አይደለም?
ግንኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ውስጥ ምርጥ የጥናት ድረ-ገጾችን እንዴት ማግኘት ይቻላል?
እኛ የምንፈልገው በይነመረቡን በምናስስ ወቅት ብቅ ብቅ የሚሉ የዳሰሳ ጥናቶች አይደሉም። እነሱ ነጻ ናቸውና ጊዜ ከማባከን በስተቀር ምንም አያመጡልንም - ምንም እንኳን ለምሳሌ ፔይፓል ወይም የስጦታ ካርዶች ቢያቀርቡም።
የዳሰሳ ጥናቶችን ለማግኝት ታማኝ የምርምር ፓነል ማግኘት አለብን፣ ይህም ለወሰድነው የዳሰሳ ጥናት የክፍያ ዋስትናን ይሰጠናል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ብዙ እንደዚህ ያሉ ገጾች በኦንላይን ይገኛሉ። የትኛውን ይመርጣሉ?
የትኛውን ይመርጣሉ?
ለአጠቃቀም ቀላል ፣ ሊነበብ የሚችል እና ከሁሉም በላይ ደግሞ የሚከፍለውን በግልፅ መምረጥ አለብዎት፤ ልክ እንደ ቲጂኤም ፓነል! እንዲመዘገቡ እና ገንዘብ ማግኘት እንዲጀምሩ እናበረታታዎታለን።
የገበያ ጥናት ምንድን ነው፣ የምርምር ኩባንያዎች ምንድን ናቸው፣ እና ምርምርስ ለምንድ ይደረጋል?
የገበያ ጥናት የመረጃ አሰባሰብ እና አተረጓጎምን ያካትታል። እነዚህ እንቅስቃሴዎች የሸቀጦች እና የአገልግሎቶች ዋጋ፣ የእነርሱ ፍላጎት እና አቅርቦት እና የሸማቾች አስተያየት እና ባህሪን ጨምሮ ሁነኛ የገበያ መሰረቶችን ለማወቅ ያስችላል። በተጨማሪም የገበያ ጥናት በገበያ ፉክክር የሚፈጠሩ ሁኔታዎችን ለመወሰን ያስችላል።
በአሁኑ ጊዜ የአንድ ድርጅት ስኬት በትንተና ላይ የተመሰረተ ነው፤ ይህም በንግድ ስራ ውስጥ ትክክለኛ ውሳኔዎችን ለመወሰን ቀላል ያደርገዋል። ስለ ገበያ መስፈርቶች ያለ እውቀት እና በትክክል የተተገበሩ የግብይት ስትራቴጂዎች አዳዲስ አገልግሎቶች እና ምርቶች እንዲፈጠሩ ያስችላቸዋል።
በተፎካካሪ ላይ የበላይነትን የሚሰጥ መረጃ የመሰብሰቢያ ቁልፍ መንገድ የገበያ ጥናት ነው።።
ስለ ድርጅቱ ስጋቶች በሚጨምሩበት ጊዜና አስፈላጊ ውሳኔዎች በሚደረጉበት ጊዜ እንዲህ ዓይነቱን ምርምር ማካሄድ ይመከራል። እንደነዚህ ያሉ ሁኔታዎች በአብዛኛው የሚከተሉትን ያካትታሉ:
- በደንበኞች ዘንድ ብዙ ተፈላጊነት ያለው ተፎካካሪ መገኘት።
- ወደ አዳዲስ ገበያዎች ለመግባት ሲታቀድ።
የሻጭ ገበያን ወደ ገዢ ገበያ መለወጥ።
በአንድ ሀገር የመንግስት የኢኮኖሚ ፖለቲካ ላይ የለውጥ ፍንጮች ሲኖሩ።
በገዢዎች መስፈርት ላይ የማያቋርጥ ለውጥ እና የፍላጎታቸው መቀነስ።
- የሙከራ ምርምር
- የዋጋ ጥናት
- የብራንድ ምርምር
- የአሰሳ ጥናት
- የደንበኛ እርካታ ጥናት
- የቤት ፓነሎች
በምርምር ዘዴዎች ምርጫ ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ ብዙ ነገሮች አሉ፤ ለምሳሌ መረጃውን ለመሰብሰብ ያለን ጊዜ፣ የምርምሩ ርዕስ መጠን፣ የፋይናንስ ወጪ እና የምርምሩ ዓላማ።
የዳሰሳ ጥናት (በዳሰሳ ጥናት ድረ-ገጾች ላይ የሚገኝ) በጣም ታዋቂ ከሆኑ የምርምር ዘዴዎች ውስጥ አንዱ ነው። በመረጃ አሰባሰቡ እና ትንተና ቅለት ምክንያት ለገበያ ምርምር መሰረታዊ መሳሪያ ሆኗል።
በበይነ መረብ ዘመን በጣም ተደራሽ እና ርካሹ የመረጃ መሰብሰቢያ ዘዴ በኦንላይን እና በሞባይል ዳሰሳ እና በዳሰሳ ጥናቱ ድረ-ገጾች ላይ ቅብብሎሽ ነው። እንዲህ ዓይነቱ ምርምር ዝቅተኛ የገንዘብ ወጪና በአንጻራዊነት ደግሞ ከፍተኛ ስፋት አለው። የኦንላይን ዳሰሳ ጥናት ጥያቄዎች ቀላል ናቸው ለእነሱ መልስ መስጠትም ለተሳታፊዎች ከባድ አይደለም።
የዳሰሳ ጥናቶቹ ሚስጥራዎነት ለተሰጡት መልሶች ተዓማኒነት ዋስትና ይሰጣል፤ ይህም ከተከናወነው ምርምር ውጤታማነት ጋር ይዛመዳል።